Dr Akililu Dental Clinic

Dr Akililu Dental Clinic For all dental problem we are here to serve you .our aim is helping our society with rec pact , love ,smile , and professional !!!

23/08/2023

ለበለጠ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉
https://t.me/Drbezaa

 #  Geesan Jedha Kiliinikii Adaa Iilkaanii Dr Akiililuu  Gadaan Kan Quufaa Gabinaa Kan Fayyaaf Gammachuu Issniif Haa Ta'...
09/09/2022

# Geesan Jedha Kiliinikii Adaa Iilkaanii Dr Akiililuu Gadaan Kan Quufaa Gabinaa Kan Fayyaaf Gammachuu Issniif Haa Ta'u Jedha Lammii Keenya Hundaaf Bari Dhufu Kun Lammii Keenyaaf Biyyaa Keenyaaf Bara Milkii Akka Issniif Ta'u Hawwa Horaa Bulaa Deebanaa Lammii Keenyaa # #

26/11/2021

የጥርስ መቦርቦር መንስኤና መፍትሄው?

https://aalemu189.wordpress.com

የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን (Cavities) እንዲፈጠሩ ያደርጋል። የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ።

✔ የጥርስ መቦርቦር እንዴት ይከሰታል?
- በጥርስ ላይ ተለጥፈው የሚቀሩ ምግቦች ካልተፀዱ ይከማቹና የባክቴሪያዎች መራቢያ እና ምግብ ይሆናሉ። ባክቴሪያዎች በሚመገቡ ጊዜ ከውስጣቸው አሲድን ይረጫሉ፣ ይህም ጥርሳችን እንዲቦረቦርና እንዲበሰብስ ያደርጋል።

✔ ለጥርስ መቦርቦር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
- ጥርስን በሚገባና በመደበኛ ሁኔታ አለማፅዳት
- ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር
- የፍሎራይድ እጥረት መኖር
- የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
- በህመም ወይንም በተለያዩ መድሀኒቶች ምክንያት የአፍ ድርቀት ሲኖር
- ሲጋራን ማጤስ ናቸው።

✔ የጥርስ መቦርቦር የሚያስከትላቸው ምልክቶች
- የጥርስ ህመም ስሜት
- በተጎዳው ጥርስ አካባቢ የድድ ማበጥ
- መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን መኖር
- በጥርስ ላይ ነጭ፣ ግራጫ፣ ቡኒ ወይንም ጥቁር ቀለማት የያዙ የተቦረቦሩ ቦታዎች መኖር ናቸው።

✔ የጥርስ መቦርቦርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
* ጥርስዎን በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጊዜ (ከቁርስ በኃላ እና ከመተኛትዎ በፊት) የፍሎራይድ ኬሚካል ባለው የጥርስ ሳሙና መታጠብ።
* በማንኛው ግዜ ምግብ ከተመገቡ በኃላ አፍዎን በንፁህ ውሀ በሚገባ መጉመጥመጥ
* ከእንቅልፍ በፊት ጥርስዎን ከታጠቡ በኃላ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ
* ጣፋጭ የበዛባቸው ምግቦችን ከምግብ ፕሮግራም ውስጥ ማስወገድ
* ልጆች ለጥርስ መቦርቦር ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም ስለ ጥርስ ፅዳት አጠባበቅ ማስተማር
* የጥርስ ሀኪምዎ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በመሄድ ጥርስዎን በባለሞያ ማሳጠብና ማስመርመር
ማሳስቢያ:

የጥርስ ህመም ሲሰማዎ ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሀኪም መሄድን አይዘንጉ ምክንያቱም የህመም ስሜቱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በራሱ ሊጠፋ ቢችልም የጥርስ መቦርቦር ግን ያለ ህመም ሊቀጥል ይችላል። በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገ ጥርስዎን እስከማጣት ሊያደርስዎ ይችላል።

ጤናዎ ጥያቄ ካሎ በቴሌግራም ቻላናችን መጠየቅ ይቻላል። መፍትሄዎችን ለምትፈልጉ የቴሌግራም ቻናላችን ተቀላቀሉ ስለሚከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን መልካም ጤንነት ተመኘውሎ
https://t.me/Drbezaa https://t.me/Drbezaa https://t.me/Drbezaa
https://t.me/Drbezaa

22/09/2021

ለመሳቅ ፈልገው ነገር ግን ፈገግታዎን በግልፅ ለማሳየት ተቸግረዋል እንግዲያውስ እንዴት አድርገው የጥርሶትን ንጣት በቤት ውስጥ እንደሚጠብቁ እንጠቁሞታል፣

የጥርስ ንጣት
¶ዘዴ 1
• ኢንጆሪ ፣
• ሎሚ እና ጨው ለጥርስ
• ½ የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ፣
• ሁለት ፍሬ የተፈጨ ኢንጆሪ ጥቂት ጨው አንድላይ በማዋሀድ የጥርስ ብሩሽላይ አድርገው መቦረሽ ይህን ማድረጋችን ጥርሳችን እንዲነጣ ከመርዳቱ ባሻገር ባክቴሪያዎችን ያስወግድልናል።

¶ ዘዴ 2
•ሙዝ ለጥርስ
•የአንድ ሙዝ ልጣጭ የውስጠኛውን ክፍል በመተቀም ጥርሳችንን በልጣጩ ለ 2ደቂቃ ማሸት ከዚያም በመደበኛ የጥርስ ሳሙና ጥርሳችንን መቦረሽ ፅድት ያለና ጥርስ ይሆናል።

ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
👇👇👇

ከኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ያገኛሉ !!

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝአድራሻዬ Dr Beza Ayalwe
https://t.me/Drbezaa
https://t.me/Drbezaa

18/09/2021

በ4 ቀን ውስጥ ጥርስን ለማንጣት የሚጠቅም ተፈጥሮኣዊው መንገድ ጥርስን ለማንጣት ተፈጥሮኣዊው መንገዶች

ዘውትር ተጠቀመው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተአምር ትመለከታለህ።
መጠን
1, ለብ ያለ ውሃ ሁለት ብርጭቆ
2, የተፈጨ ቀረፋ አንድ ማንኪያ
3, የንብ ማር አንድ ማንኪያ
4, የሎሚ ጠብታዎች
☞አዘገጃጀት☜
ተለቅ ባለ ብርጭቆ ውሃውን እንጨምራለን። ከዚያም ቀረፋውን እና ማሩን እናስከትላለን። በመጨረሻም ከአምስት የማይበልጡ የሎሚ ጠብታዎችን እንጨምርበትና በደንብ አዋህደን ስናበቃ ዘውትር ጠዋት አፋችንን እንጉመጠመጥበታለን።

ለውጡን በ4 ቀናት ውስጥ ቁልጭ አድርጎ ያሳይወታል::

ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
👇👇👇

ከኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ያገኛሉ !!

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝአድራሻዬ Dr Beza Ayalwe
https://t.me/Drbezaa
https://t.me/Drbezaa

14/09/2021

መጥፎ የአፍ ጠረን በምን ይከሰታል? መከላከያውና መፍትሄዎቹስ?
---------------------------------------------------------
የመጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤው ምንድንነው?

መጥፎ የአፍ ጠረንን አስመልክቶ የተፃፉ አብዛኞቹ መረጃዎች መንስኤዎቹን በሁለት ከፍለው ይተነትኑታል፡፡ በቅድሚያ ከአፍ ውስጥ አካላት ጋር በተያያዙ ችግሮች እና የአፍ ውስጥ ንፅህና ባለመጠበቅ የሚመጣ መጥፎ የአፍ ጠረን ነው። ይህም የሚሆነው የአፍ እና የጥርስ ንፅህና በአግባቡ በማይጠበቅበት ጊዜ የምግብ ሽርፍራፊዎች በጥርስ እና በድድ መሃል እንዲሁም በጥርስ እና በጥርስ መካከል ሲከማቹ ጎጂ ባክቴሪያዎች ከምራቅ ጋር በመዋሀድ እነዚህን የምግብ ቅሪቶች እንዲሰባበሩ ስለሚያደርጉ ነው፡፡ ይህም ሂደት በሚከናወንበት ጊዜ የሚለቀቀው የሰልፈር ጋዝ መጥፎ የአፍ ጠረንን ያስከተላል፡፡

በመሆኑም ከሚከተሉት በአንዱም ሆነ በሌላው መንገድ የአፋችን ንፅህና ካልተጠበቀ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊኖር ይችላል። እንደጥርሳችን ሁሉ ምላሳችንም ባግባቡ ፅዳቱ ካልተጠበቀ ብዙ ሸካራ እና ወጣ ገባ ያሉ ቦታዎች ስላሉት የምግብ ቅሪት እና ባክቴሪያዎች በቀላሉ አጠራቅሞ መጥፎ ጠረን ሊፈጥር ይችላል፡፡

አፋችን ውስጥ የተቦረቦረ ጥርስ ካለ በውስጡ ምግብ እና ባክቴሪያ ሊይዝ ስለሚችል ይህም መጥፎ ጠረን ሊያመጣ ይችላል፡፡ አፋችን ውስጥ የሰው ሰራሽ ጥርስ ካለና ይህ ጥርስ ባግባቡ ከድድ ጋር ካልገጠመ በመካከል ምግብ እና ባክቴሪያ ሊይዝ ስለሚችል የመጥፎ ጠረን መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡ በድድ እና በጥርስ አቃፊ አካላት ላይ የጤንነት መጓደል ካለና የድድ መሸሽ፣ በጥርስ አቃፊ አካላት መካከል ክፍተት(periodontal pocket) ካለ ይህም ለምግብ እና ባክቴሪያ መከማቸት ዕድል ስለሚሰጥ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የአፍ መድረቅ ለአፋችን ንፅህና ምራቅ እራሱን የቻለ አስተዋፅኦ አለው። ይህም ማለት ምራቅ በበቂ መጠን አፋችን ውስጥ ካለ ያሉትን የባክቴሪያ እና የምግብ ቅሪቶች በማንሸራተት ወደ ውስጥ በመላክ ጠረን እንዳይፈጥሩ ይከላከላል፡፡ ምራቅ በተገቢው መንገድ ሳይመነጭ ቀርቶ አፍ ከደረቀ ግን ለባክቴሪያ ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጣ ይችላል፡፡ የጉሮሮ፣ የእንጥል፣ የድድ፣ እንዲሁም የምላስ መቁሰል ወይም ኢንፌክሽን ካለ መጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡ ሲጋራ ማጨስና መጠኑ የበዛ አልኮል ማዘውተርም መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጣ ይችላል። እንዲሁም በተፈጥሮ ከባድ ሽታ ያላቸው ምግቦች ለምሳሌ እንደ ቀይ እና ነጭ ሽንኩርት ያሉትን ምግቦች መጠቀም ጊዜያዊ የሆነ የአፍ ጠረን ለውጥ ሊያስከትል ይችላል። ምንም እንኳ እነዚህ ምግቦች የሚያመጡት መጥፎ ጠረን ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ በራሱ የሚጠፋ ቢሆንም፡፡

ሁለተኛው ከአፍ ውጪ ባሉ ችግሮች የሚመጣ የአፍ ጠረን ሲባል በውስጣዊ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ በሚኖር በሽታ ምክንያት የሚከሰተውን የአፍ ጠረን ለውጥ ለማመላከት ነው፡፡ አንድ ሰው የኩላሊት፣ የስኳር፣ የጨጓራ ወይንም የጉበት በሽታ ካለበት ከበሽታው ጋር ተያይዞ የሚኖር የአፍ ጠረን ለውጥ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንዴ የትንፋሽ ጠረን ለውጥ የውስጣዊ ችግሮች ጠቋሚ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ግን ማስተዋል ያለብን መጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤ ውስጣዊ በሽታ ሊሆን ይችላል ሲባል ማንኛውም መጥፎ የአፍ ጠረን ያለበት ሰው ሁሉ ውስጣዊ ችግር አለበት ማለት እንዳልሆነ መረዳት ይገባል፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረን መፍትሔ መጥፎ የአፍ ጠረን ሕክምና በትክክል መፍትሔ ሊያመጣ የሚችለው የጠረኑ መንስኤ በአግባቡ ተለይቶ ታውቆ ተገቢው ሕክምና እስከተደረገ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ከአፍ ውስጥ አካላት ጉድለቶች ጋር በተያያዘ የሚመጣ የአፍ ጠረን ትክክለኛው ሕክምና ከተደረገለት ሙሉ ለሙሉ የመዳን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው ተጠቂው ሐኪም ጋር ቀርቦ ጉድለት የደረሰበትን አካል ሲታከም ነው፡፡ ማለትም የተቦረቦረ ጥርስ ካለ በመሙላት፣ የተከማቸ ቆሻሻ ካለ በማንሳት፣ የአፍ ውስጥ ኢንፌክሽን ካለ በተገቢው መንገድ በማከም እንዲሁም ውስጣዊ የጤና እክልን በሕክምና በማስወገድ ይሆናል፡፡ የአፍ ውስጥ አካላት ችግሮች ተፈተው ጠረኑ ቀጣይነት ካለው ከውስጣዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ ሊሆን ስለሚችል ውስጣዊ አካላት ላይ ምርመራ አካሂዶ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በስተመጨረሻ የአፍ ጠረን ቢኖርም ባይኖርም ስለ ጥርስና አፍ ጤና አጠባበቅ ዘዴዎች በጤና ባለሙያዎች የተለያዩ ምክሮች ይሰጣሉ። ጠዋትና ማታ የጥርስ ሳሙና ተጠቅሞ በበቂ ሁኔታ ጥርስን ማፅዳት፣ የምንጠቀምበት ሳሙና የአገልግሎት ዘመኑ አለማለፉን ማጤን አስፈላጊ ነው። ሁሉንም የጥርስ ቦታዎች በለስላሳ ቡርሽ ከድድ ወደ ጥርስ መቦረሽ፣ ጥርስ ተጸድቶ ካለቀ በኋላ ምላስን ከኋላ ወደ ፊት በደንብ ማጽዳት፣ ከብሩሽ በተጨማሪ የጥርስ ማጽጃ ክር (dental floss) ተጠቅሞ ጥርስን ማፅዳት፤ በሐኪም የታዘዘ የአፍ መጉመጥመጫ ፈሳሽ ካለ በአግባቡ መጠቀም፤ ከስኳር ነፃ የሆኑ ማስቲካዎችን ማኘክ ይህም የምራቅ መመንጨትን ስለሚያበረታታ አፍን ጽዱ የማድረግ አቅም አለው። በተጨማሪም ምግብ ከተመገብን በኋላ አፍን በንጹህ ውሃ መጉመጥመጥ፣ ሲጋራ አጫሽ ከሆኑ ጭሱ የሚያመጣውን ውጫዊ የቀለም ለውጥ ሊያነሱ የሚችሉ ልዩ የጥርስ ሳሙናዎች ስላሉ እነርሱን መጠቀም ይገባል።

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Telephone

251911-39-15-48

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Akililu Dental Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share