Dr. Meron Hailemariam

Dr. Meron Hailemariam ስለ አፍ እና ጥርሳችሁ ጤና መረጃ አቀብላችኋለሁ ስለ እናንተም ሆነ ስለ ልጆቻችሁ ጥርስ መረጃ የምታገኙበት እና ጥያቄ መጠየቅ የምትችሉበት ነው

ክሊኒካችን ሰበን ልዩ የጥርስ ህክምና CAD/CAM 5X system በማስመጣት የሙከራ ግዜያችንን ጨርሰን ወደ ስራ ገብተናል ዚርኮኒያ ጥርስ ለማድረስ የሚፈጅብንም 36 ሰዓት ብቻ ነው
10/03/2024

ክሊኒካችን ሰበን ልዩ የጥርስ ህክምና CAD/CAM 5X system በማስመጣት የሙከራ ግዜያችንን ጨርሰን ወደ ስራ ገብተናል ዚርኮኒያ ጥርስ ለማድረስ የሚፈጅብንም 36 ሰዓት ብቻ ነው

በአንድ ቀን ፍንጭት መዝጋትDiastema closure by single visit                SEBEN Speciality Dental Clinic
27/08/2023

በአንድ ቀን ፍንጭት መዝጋት
Diastema closure by single visit
SEBEN Speciality Dental Clinic

Resin filling done in a single visit @ seben dental0911248702 for your appointment
03/12/2022

Resin filling done in a single visit @ seben dental
0911248702 for your appointment

30/11/2022

Bleaching done SEBEN Speciality Dental Clinic

Jacket by Zirconium crown. For appointment ☎️ 0911248702
25/11/2022

Jacket by Zirconium crown.
For appointment ☎️ 0911248702

Our clinic is going digital by adding panoramic X-ray. This will make our diagnosis very easy and precise.
07/11/2022

Our clinic is going digital by adding panoramic X-ray. This will make our diagnosis very easy and precise.

ስለ ልጆቻችን ጥርስ ጤና አጠባበቅ ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ስር አስቀምጡልኝ በተቻለኝ አቅም ለመመለስ እሞክራለሁ ለዛሬ ግን በአጠቃላይ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን እናያለን- ጥርሳቸ...
27/10/2022

ስለ ልጆቻችን ጥርስ ጤና አጠባበቅ ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ስር አስቀምጡልኝ በተቻለኝ አቅም ለመመለስ እሞክራለሁ ለዛሬ ግን በአጠቃላይ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን እናያለን
- ጥርሳቸውን በየእለቱ ማፅዳት
- ጥርሳቸውን መቼ ማፅዳት እንጀምር? አንድ ጥርስ ካበቀሉ ጀምሮ
- አንድ ግዜ ስናፀዳ 2 ደቂቃ ወስዶ በደንብ ማፅዳት
- መክሰሳቸውን ጤናማ የሆነ ምግብ እንዲመገቡ ማድረግ
- ፈሳሽ ነገር በደንብ እንዲጠጡ ማድረግ
- የጥርስ ብሩሻቸውን ከ3-4 ወር ባለው ግዜ መቀየር
- በየግዜው ቼክ አፕ እንዲኖራቸው ማድረግ
እነዚህን ነገሮች ካደረግን ልጆቻችን ጤነኛ የሆነ ጥርስ ይኖራቸዋል ጤነኛ አመጋገብም ይኖራቸዋል።

23/06/2022

የጥርስ እጥበት ቢቻል በአመት ሁለት ግዜ ባይቻል ደግሞ አንድ ግዜ ቢደረግ ይመከራል

መጥፎ የአፍ ጠረን (Halitosis)በጣም በተደጋጋሚ በመልእክት የምጠነቀው ጥያቄ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ ምን ባደርግ ይሻለኛል የሚለውን ነው ይኸው ሙሉ መረጃ ይዤላችሁ መጥቻለውመጥፎ የአ...
03/06/2022

መጥፎ የአፍ ጠረን (Halitosis)

በጣም በተደጋጋሚ በመልእክት የምጠነቀው ጥያቄ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ ምን ባደርግ ይሻለኛል የሚለውን ነው ይኸው ሙሉ መረጃ ይዤላችሁ መጥቻለው

መጥፎ የአፍ ጠረን የአለማችንን 25% የሚሆን ማህበረሰብ ያጠቃል። ለችግሩ ብዙ መነሻ ምክንያቶች ቢኖሩም አብዛኛውን ግዜ መነሻው ከአፋችን ነው።

ስለ መጥፎ የአፎ ጠረን (ሐሊቶሲስ/ halitosis) እውነታዎች

-መጥፎ የአፍ ጠረን ከ4 ሰዎች በአንዱ ላይ ይከሰታል
-አብዛኛው መነሻ ምክንያቱ የጥርስ እና የአፋችንን ንፅህና (oral hygiene) በደንብ ባለመጠበቅ የሚመጣ ነው።
-የበላነው ምግብ አፋችን ውስጥ ይቀእና ሰልፈር ወደሚባለው ንጥረ ነገር በባክቴሪያ ምክንያት ተከፋፍሎ መጥፍ የአፍ ጠረን ያመጣል
-ዋናው በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችለው ህክምናም ጥርሳችንን ማፅዳት፣ ፍሎስ ማድረግ እና በቂ የሆነ ውሀ መጠጣት ናቸው።

መጥፎ የአፍ ጠረን (halitosis) ምንድን ነው?
መጥፎ የአፍ ጠረን በጣም የተለመደ እና በራስ መተማመንን የሚቀንስ በሽታ ነው። በጣም ብዙ መነሻ ምክንያቶች እና መፍትሄዎችም አሉት። ማንኛውም ሰው መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያጋጥመው ይችላል። ከ4 አንድ ሰው ላይም ያጋጥማል። ወደ ጥርስ ሀኪም ከሚያስኬዱ መነሻ ምክንያቶችም 3ኛ ነው። ከጥርስ መቦርቦር እና ከድድ ችግር ቀጥሎ
አንዳንድ በቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮች ለምሳሌ ጥርሳችንን እና አፋችንን ማፅዳት ፣ ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም ጫት መቃም ማቆም ችግሩን እስከነአካቴው ያቆሙልናል ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ወደ ጥርስ ሀኪም መሄድ ያስፈልጋል።

ህክምናው
_ለመጥፎ የአፍ ጠረን ዋናው ህክምና ጥሩ የሆነ የጥርስ እና የአፍ ማፅዳት ልማድን (good oral hygiene) ማዳበር ነው። ተያይዞም ጥርሳችን እንዳይቦረቦር እና ድዳችን እንዳይጎዳ ይረዳናል።

_በአመት ቢቻል አንድ ግዜ የጥርስ ቼክ አፕ ማድረግ

_የጥርስ ሀኪምዎ ባክቴሪያን የሚቀንሱ መጉመጥመጫዎች ሊያዝሎት ይችላል እንዲሁምየጥርስ እጥበት እንዲያደርጉ ሊመክሮት ይችላል።

መነሻ ምክንያቶች
- ሲጋራ
- ምግብ ፦ የበላነው ምግብ ጥርሳችን ላይ ተጣብቆ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጣብን ይችላል። በተለይ ቀይ እና ነጭ ሽንኩርት ከተፈጨ በኋላ እንኳን በደም ስራችን አልፎ ወደ ሳንባችን ደርሶ ስንተነፍስ ሊሸት ይችላል።
- ደረቅ አፍ( dry mouth)፦ በተፈጥሮ ምራቃችን አፋችንን ያጥብልናል። አፋችንን ደረቅ ከሆነ ግን መጥፎ የአፍ ጠረን ይከሰታል።
- ጥርሳችንን እና አፋችንን የማፅዳት ልማድ፦ ጥርሳችንን በምንቦርሽበት እና ፍሎስ በምናደርግበት ግዜ አፋችን ውስጥ ያለው ምግብ ተፀድቶ ይወጣል ካልወጣ ግን በባክቴሪያዎች አማካኝነት ተከፋፍሎ ችግሩ እንዲከሰት ያደርጋል።
- የምግብ ሰዓትን ጠብቆ አለመብላት፦ መፆም እና ካርቦሀይድሬት ያነሳቸውን ምግቦችን መመገብ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖረን ያደርጋል ምክንያቱ ደግሞ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ስብሰባብሮ ሲጠቀም ኬቶን(ketones) የሚባል ኬሚካል ያመነጫል ይህም ከፍተኛ ሽታ የመጣል።
- መድሀኒቶች፦ አንዳንድ መድሀኒቶች አፋችን እንዲደርቅ ያደርጋሉ ሌሎች ደግሞ ሲሰባበሩ የራሳቸው የሆነ ሽታ ይፈጥራሉ።
- የአፍ የአፍንጫና የጉሮሮ ችግር፦ አንዳንድ ግዜ ትንንሽ ባክቴሪያዎች ከቶንሲላችን ጀርባ እንደ ድንጋይ ተሰባስበው ይገኙና መጥፎ ጠረን ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአፍንጫ የጉሮሮ ወይም የሳይነስ ኢንፌክሽን እና መቆጣት የአፍ ጠረን ሊያመጣ ይችላል።
- የውስጥ በሽታ፦ አንዳንድ ካንሰር ፣ የጉበት ስራ ማቆም(liver failure) እና ሌሎች ከምግብ መፈጨት ጋር የተገናኙ በሽታዎች የአፍ ጠረን ሊያመጡ ይችላሉ ምክንያቱ ደግሞ የሚፈጥሩት ኬሚካሎች ናቸው። እንዲሁም የጨጓራ ህመም Gastroesophageal Reflux Diseases(GERD) በሚለቀው የጨጓራ አሲድ ምክንያት መነሻ ሊሆን ይችላል።

ከስንት አንድ መነሻ ምክንያቶች
አብዛኛው መጥፎ የአፍ ጠረን መነሻ ምክንያት የአፋችንን ንፅህና በደንብ አለመጠበቅ ቢሆንም ሌሎች መነሻ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ።

1- Ketoacidosis(ኬቶአሲዶሲስ)፦ አንድ ስኳር ህመም ያለበት ሰው ኢንሱሊኑ ዝቅ ሲል ሰውነታቸው ውስጥ ያለውን ስኳር መጠቀም ያቆምና የተጠራቀመውን ስብ ይጠቀማል። ስቡም ሲሰባበር ኬቶን(ketones) ይመረታል ይህም ሲበዛ መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣል እንዲሁም ለህይወት አስጊ የሆነ ጉዳይ ነው።

2- Bowl obstruction (የአንጀት መደፈን)፦ ትንፋሻቸው ሰገራ ሰገራ ሊል ይችላል በተለይ በተደጋጋሚ ማስመለስ ካለ እና የአንጀት መደፈን ካለ።

3- Bronchiectasis(ብሮንካይተስ)፦ የአየር ቧንቧችን ለረጅም ግዜ ኢንፌክሽን ካጋጠመው ሊሰፋና ሙከስ ተጠራቅሞ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ሊዳርገን ይችላል።

ምልክቶች

×የአፍ ጠረን ሽታው እንደመነሻ ምክንያቱ ይለያያል። እርግጠኛ ለመሆኖ ጥሩ የሚሆነው ጓደኛችንን ወይም ቅርብ የምንለውን ሰው መጠየቅ ነው ምክንያቱም በራሳችን ለማወቅ እና እርግገኛ ለመሆን ከባድ ስለሆነ።

× ማንም ሰው አጠገባችን ከሌለ በእጃችን በደንብ ተንፍሰን ደረቅ እስኪል ጠብቀን ማሽተት ነው።

× አንዳንድ ሰዎች ግን ምንም አይነት መጥፎ የአፍ ጠረን ሳይኖርባቸው እንዳለባቸው ይሰማቸዋል ይህም halitophobia (ሀሊቶፎቢያ) ይባላል ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ጥርሳቸውን የሚያፀዱ ሰዎች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

እቤት ውስጥ ምን እናድርግ?
፩- ጥርሳችንን ማፅዳት፦ በቀን ቢያንስ 2 ግዜ ለ2 ደቂቃ ተገቢ በሆነ ሁኔታ ጥርሳችንን ማፅዳት

፪- ፍሎስ ማድረግ፦ ፍሎስ ማድረግ በጥርሶቻችን መሀከል የሚጠራቀመውን ምግብ እና ፕላክ ያወጣልናል። በብሩሽ ስናፀዳ የምናገኘው 60% የሚሆነውን የጥርሳችንን ክፍል ነው።

፫- ወጪገቢ ጥርስ፣ አርቴፊሻል፣ ማውዝ ጋርድ፣ ሪቴነር ካለን በየእለቱ ማፅዳት

፬- የጥርስ ብሩሻችንን በየ3 ወሩ መቀየር

፭- ስስ(soft) የጥርስ ብሩሽ መጠቀም

፮- ምላሳችንን ማፅዳት፦ ምላሳችንን ሳሙና በሌለው ብሩሽ በአፍንጫችን እየተነፈስን ማፅዳት ለራሱም የተዘጋጀውን ማፅጃ ካገኘን መጠቀም በተለይ ደግሞ ሲጋራ የሚያጨሱ ፣ ጫት የሚቅሙ እና የአፍ መድረቅ ችግር ያለባቸው ሰዎች ምላስን በደንብ ማፅዳት ያስፈልጋል።

፯- አፋችን እንዳይደርቅ ማድረግ፦ ውሀ በተገቢው መንገድ በደንብ መጠጣት። የአልኮል መጠጥ ሲጋራ እና ጫት ማስወገድ ምክንያቱምየአፍ መድረቅ ስለሚያመጡ። ማስቲካ ማላመጥም ምራቅ እንዲመረት ስለሚረዳ ይመከራል ከተገኘ ስኳር የሌለው።

፰- አመጋገብ፦ ቀይ ሽንኩርት ነጭ ሽንኩርት እና ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች ማስወገድ። ጣፋጭ ምግቦችም ከመጥፎ የአፍ ጠረን ጋር ይያያዛሉ። ቡና እና የአልኮል መጠጦችን መቀነስ። ቁርስ ላይ ጠንከር ያለ ምግብ መመገብ የምላሳችን ጀርባ እንዲያፀዳ ይረዳዋል።

ምርመራ

አብዛኛውን ግዜ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ ብሎ የመጣን ታካሚ በማሽተት እና ከምላስ ጀርባ ፍቆ በማሽተት ሊታወቅ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች የተወሳሰቡ ምርመራዎች አሉ።
የጥርስ ሐኪማችን የመጥፎ አፍ ጠረን መነሻ ምክንያቱን ያገኝልናል። መፍትሄም ይኖረዋል።

አብዛኛውን ግዜ መጥፎ የአፍ ጠረን ከተከሰተብን በኋላ ከላይ ያሉትን ነጥቦች ከተከተልን በቤት ውስጥ ጥንቃቄ ራሱ የሚጠፋ ይሆናል ይህ ካልሆነም የጥርስ ሐኪሞን ማማከር ያስፈልጋል።
አንዳንድ ግዜ መጥፎ የአፍ ጠረን ባይኖርባቸውም በስራ ቦታችን ብዙ የሚመላለሱ ሰዎች አሉ በተለይ ደግሞ ሰው አንድ ግዜ ከነገራቸው ግን መረዳት ያለብን ዋናው ነገር በሽታው ወደ ቦታው መመለስ የሚችል (reversible) መሆኑን ነው።

ዶ/ር ሜሮን ኃ/ማርያም
ሲንየር ዴንታል ሰርጅን

የአፍዎን እና የጥርስዎን ጤና በቀን 2 ግዜ በማፅዳት ይጠብቁ
01/06/2022

የአፍዎን እና የጥርስዎን ጤና በቀን 2 ግዜ በማፅዳት ይጠብቁ

Single visit composite filling.
27/05/2022

Single visit composite filling.

Address

Djibuti Street
Addis Ababa

Telephone

+251911248702

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Meron Hailemariam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr. Meron Hailemariam:

Share