Dr Mohammed Dental Clinic ዶ/ር መሀመድ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ

  • Home
  • Ethiopia
  • Tepi
  • Dr Mohammed Dental Clinic ዶ/ር መሀመድ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ

Dr Mohammed Dental Clinic   ዶ/ር መሀመድ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ healthy tooth for better smile! prevention is better than cure
(2)

ጥርስ ማንጣት ይፈልጋሉ? በተለያዩ ነገሮች የበለዙ ጥርሶችን ዘመናዊ ማሽን በመጠቀም ማንጣት ጀምረናል። ኑ !!!!
17/04/2025

ጥርስ ማንጣት ይፈልጋሉ?
በተለያዩ ነገሮች የበለዙ ጥርሶችን ዘመናዊ ማሽን በመጠቀም ማንጣት ጀምረናል። ኑ !!!!

የአፍ ውስጥ ካንሰርየአፍ ውስጥ ካንሰር በአፍ ውስጥ ማለትም በከንፈር፣ በድድ፣ በላንቃ፣ በምላስና ከምላስ ስር እንዲሁም በጉንጭ በውስጠኛ ክፍል ውስጥ ይከሰታል።በአፍ ውስጥ የሚከሰት ካንሰር ...
10/05/2024

የአፍ ውስጥ ካንሰር

የአፍ ውስጥ ካንሰር በአፍ ውስጥ ማለትም በከንፈር፣ በድድ፣ በላንቃ፣ በምላስና ከምላስ ስር እንዲሁም በጉንጭ በውስጠኛ ክፍል ውስጥ ይከሰታል።

በአፍ ውስጥ የሚከሰት ካንሰር 95% የሚሆነው aquamous cell carcinoma በመባል ይታወቃል ቀሪው 5% በመቶ ሎሎች አይነት ካንሰሮች /melanoma,salivary gland cancers ወዘተ ናቸው።

የአፍ ውስጥ ካንሰር ከ100,000 ሰው 11.5ስዎችን እንደሚያጠቃ የናሽናል ካንሰር ሰርቬይ ያሳያል። ከሴቶች አንፃር ወንዶች ላይ ሶስት እጥፍ ይከሰታል:: ከጥቁሮች ይልቅ ነጮች ላይ እንዲሁም እድሜ እየጨመረ ሲሄው በካንሰር የመያዝ እድል እየጨመረ ይሄዳል።

ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?

የጥርስ በድንገት መንቀሳቀስና የጉንጭና የታችኛው መንጋጋ ድንዛዜ

የጉንጭ የውስጠኛው ክፍል ላይ የሚታዩ ነጭና ቀይ እንዱሁም ህመም ያላቻው ምልክቶች

የሚታይ በፍጥነት የሚያድግ እባጭ

ከሁለት ሳምንት የበለጠ በአፍ ውስጥ የሚቆይ ቁስለት

በግዜ ሂደት ምላስን ለማንቀሳቀስ ማዳገት

የሚደማ የማይድን ህመም ያለው የአፍ ውስጥ ቁስለት

ለመዋጥ መከልከል

በአንገት አከባቢ የንፍፊት ማበጥ

የጆሮና የጥርስ ህመም

አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸው?
ሲጋራ ማጤስ
አልኮል ማዘውተር
የፀሀይ ብርሀን ከንፈር ላይ በተደጋጋሚ ማረፍ
የHPV ኢንፌክሽን
የአፍ ንፅህና ጉድለት
የተሰባበሩና የሚወጉ ጥርሶች በአፍ ውስጥ መኖር (በተደጋጋሚ ጉንጭ ላይ ቁስለት ካንሰር ሊያስከትል ይችላል)
ሌሎች ቅድመ ካንሰር የአፍ ውስጥ ህመሞች (erthroplakia leukoplakia,lichen planus)
የቆየና በተደጋጋሚ የሚከሰት የፈንጋስ ህመም

እንዴት መከላከል ይቻላል?

ሲጋራና አልኮል ማስወገድ
የፈንገስ ህመም ተክታትሎ መታከም
የፀሀይ ብርሀን በተደጋጋሚ የሚያገኛቸውን የሰውነት ክፍል መሸፈን (sunscreen, ኮፍያ ፣ ዣንጥላ)

በተለይ ለሁለት ሳምንትና ከዛ በላይ የቆየ የአፍ ውስጥ ቁስለት በፍጥነት መታከም።

የአፍን ጤንነት በአመት 2 ግዜ በአኪም ማወቅ ወሳኝ የመከላከያ ዘዴዎች ናቸው።

Source :Telegram: t.me/HakimEthio

08/05/2024

ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈጠር ህመም | Alveolar Ostitis also called Dry socket

ጥርስ በተለያዩ ምክንያቶች ሊነቀል ይችላል ከተነቀላ በኋላ ግን የከፋ ህመም በብዙ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ይህም የሚፈጠረው ሐኪምዎ እንዲተገብሩ ያዘዝዎትን ትዛዝ ሳያከብሩ ሲቀሩ፣ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰዓት ጥርስ የሚነቀሉ ከሆነ፣ የወሊድ መቆጣጠርያ መድኃኒት እየወሰዱ የሚነቀሉ ከሆነ፣ ጥርስ ከተነቀለ በኋለ በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምባሆ የሚያጨሱ ከሆነ የተባለው ህመም ሊከሰት ይችላል።

የህመሙ ዓይነት የሚጠዘጥዝ ህመም ሲሆን የተነቀለበት ቦታ ቁስሉ ወደ ግራጫ መልክ የመቀየር፣ የአፍ ጠረን የማምጣት እና ብሎም እብጠትም ጭምር ሊኖረው ይችላል።

ነገር ግን ጥርስ ከተነቀለ በኋላ ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ ዓይነቶች አሉ እነሱም

1. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያን ለ 30 ደቂቃ ያህል ሐኪምዎ ያስነከሰዎትን ጥጥ በተነቀለበት ቦታ ነክሰው ማቆየት

2. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ትኩስ ነገር መብላትም ሆነ መጠጣት አይመከርም መመገብ ካለብዎ በረድ ወይም ለብ ያለ ነገር መሆን አለበት

3. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ደምም ይሁን ምራቅ መዋጥ እንጂ መትፋት በፍፁም የተከለከለ ነው

4. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት የትኛውም ዓይነት ፈሳሽ ነገር ሲጠጡ መምጠጫ(Straw) መጠቀም አይመከርም

5. ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጥርስ የተነቀለበትን ቦታ በእጅ፣ በምላስ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች መነካካት አይመከርም

6. ምግብ ከበሉ በኋላ የበሉት ምግብ በቁስሉ በመከማቸት ለኢንፌክሽን የማጋለጥ ዕድሉ የሰፋ ስለሆነ እንደተመገቡ ጨው በውኃ በመቀላቀል ለብ አድርገው ተጉሞጥምጦ መትፋት

7. ቁስሉ እንዲድን አጋዥ ይሆናሉ ተብሎ በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶች ካሉ በትዕዛዙ መሰረት መውሰድ

8. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያንስ ለተከታታይ 10 ቀናት ትምባሆ ማጨስ አይመከርም።

9. ከላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዛት ሁሉ ተግብረው ነገር ግን ህመም እየበረታ ከሔደ እና እብጠት ካመጣ ፈጥነዉ ሐኪምዎትን ያማክሩ።

እነዚህን ትዕዛዛት ከተገበሩ ሊመጣ የሚችለውን ህመም መከላከል ይችላሉ።

Dr Mohammed, Senior Dental Surgeon

የአፍ ጤናን በመጠበቅ የስኳር ህመምን መቆጣጠር እንዲሁም አጠቃላይ የሰውነትን ጤንነት ለማጎልበት ቁልፍ መሆኑን ያውቃሉ?ከፍተኛ የስኳር መጠን በአፍና በሰውነት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በጋራ ...
27/01/2024

የአፍ ጤናን በመጠበቅ የስኳር ህመምን መቆጣጠር እንዲሁም አጠቃላይ የሰውነትን ጤንነት ለማጎልበት ቁልፍ መሆኑን ያውቃሉ?

ከፍተኛ የስኳር መጠን በአፍና በሰውነት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በጋራ እንከላከል!

ይህንን መረጃ ለሚወዷቸው ወዳጆችዎ ያጋሩ!

ጥርስ ከተነቀሉ በኋላ ምን መደረግ አለበት???- የነከሱትን ጥጥ ለ 40 ደቂቃ በቦታው መያዝ- ለ 24 ሰዓት ምራቅ አለመትፋት- ለ 24 ሰዓት ትኩስ ነገር አለመውሰድ- ለ 24 ሰዓት አለመጉመ...
21/01/2024

ጥርስ ከተነቀሉ በኋላ ምን መደረግ አለበት???

- የነከሱትን ጥጥ ለ 40 ደቂቃ በቦታው መያዝ
- ለ 24 ሰዓት ምራቅ አለመትፋት
- ለ 24 ሰዓት ትኩስ ነገር አለመውሰድ
- ለ 24 ሰዓት አለመጉመጥመጥ
- ጥርሱ የወለቀበት ቦታን በእጅም ሆነ በምላስ አለመንካት
- ከ 24 ሰዓት በኋላ ለብ ያለ ውሃ ላይ ቲኒሽ ጫው አድርጎ መጉመጥመጥ ( ይህም ቁስሉ ቶሎ እንዲድን ያደርገዋል )
- የታዘዘሎትን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ
- የመድማት ችግርና ከባድ ህመም ከገጠመዎት ሐኪምዎን ያማክሩ።

14/01/2024
ብዙውን ጊዜ ጥርሳችንን በምንቦርሽበት ወቅት የሚታየው የድድ መድማት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። የተለመደው መንስኤ በአፍ ንፅህና አጠባበቅ ምክንያት የሚከሰት የድድ እብጠት ነው። የ...
14/01/2024

ብዙውን ጊዜ ጥርሳችንን በምንቦርሽበት ወቅት የሚታየው የድድ መድማት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል።

የተለመደው መንስኤ በአፍ ንፅህና አጠባበቅ ምክንያት የሚከሰት የድድ እብጠት ነው። የሆርሞን ለውጦች፣ መድሃኒቶች፣ የህክምና ሁኔታዎች፣ የቫይታሚን እጥረት እና ጭንቀት ለድድ መድማት አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይችላሉ ።

ይህንን ችግር ለማስቀረት የአፍ ንፅህና ለመጠበቅ አዘውትው መቦረሽ እና መፋቅ፣ ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ መጠቀም እና የጥርስ ሀኪምን መጎብኘት ናቸው። በተጨማሪም የተመጣጠነ አመጋገብ፣ ጭንቀትን መቆጣጠር እና ማጨስ ማቆም የድድ መድማትን ለመከላከል ተጨማሪ እገዛ ያደርጋል። ችግሩ ከቀጠለ ለትክክለኛውን ምርመራ ወደ የጥርስ ሐኪም በመሄድ ያድርጉ።

አጥንት ወስጥ ተቀብረው የቀሩ ጥርሶች Impacted teethየተቀበረ ጥርስ በሆነ ምክንያት ድድን ከፍቶ ለመውጣት ያልቻለ  ጥርስ ነው። አንዳንድ ጊዜ አንድ ጥርስ በከፊል ብቻ ድድን ከፍቶ ወ...
07/01/2024

አጥንት ወስጥ ተቀብረው የቀሩ ጥርሶች Impacted teeth

የተቀበረ ጥርስ በሆነ ምክንያት ድድን ከፍቶ ለመውጣት ያልቻለ ጥርስ ነው። አንዳንድ ጊዜ አንድ ጥርስ በከፊል ብቻ ድድን ከፍቶ ወደ ኣፍ ብቅ ሊል ይችላል ፣ ከፊል መቀበር (partial or secondary impaction) የሚባል ዓይነት።

ብዙውን ጊዜ ፣ ​​የተቀበሩ ጥርሶች ምንም ግልጽ ምልክቶች አያሳዩም እና ብዙውን ጊዜ ሀኪምዎ በኤክስሬይ ሊያገኛቸው ነው የሚችለው።

የተቀበሩ ጥርሶች ምልክቶች

በአንዳንድ ሁኔታዎች የተቀበረ ጥርስ የሚከተሉትን ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል-
✅ ቀይ ፣ ያበጠ ወይም የድድ መድማት የተቀበረው ጥርስ ዙሪያው ላይ
✅ መጥፎ የአፍ ጠረን
✅ መጥፎ ጣዕም በአፍዎ ውስጥ
✅ አፍዎን ለመክፈት ችግር
✅ አፍዎን ሲከፍቱ ፣ ወይም ሲያኝኩ እና ሲነክሱ ህመም

ምልክቶቹ ከሳምንታት ወይም ከወራት በላይ ሊመጡ እና ሊሄዱ ይችላሉ።

የተቀበረ ጥርስ ምን ያስከትላል?
በአጠቃላይ ፣ አፍዎ ለእሱ በቂ ቦታ በማይኖርበት ጊዜ ጥርስ ተቀብሮ ሊቀር ይችላል። ይህ የጄኔቲክስ ወይም የአጥንት አለማደግ ውጤት ሊሆን ይችላል።

የትኞቹ ጥርሶች ብዙውን ጊዜ ይቀበራሉ?

ብዙውን ጊዜ የሚያድጉ የመጨረሻ ጥርሶች የሆኑት (wisdom tooths) ጥርሶች - በተለምዶ ከ 17 እስከ 21 ዓመት ባለው ዕድሜ ክልል ሊበቅሉ ይችላሉ። የመጨረሻ ጥርሶች ወይም wisdom tooths በመባልም ይታወቃሉ - በሚያድጉበት ጊዜ መንጋጋ ብዙውን ጊዜ ማደግ ያቆማል።

ስለዚህ አፍ እና መንጋጋ እነሱን ለማስተናገድ በጣም ትንሽ ሊሆኑ ይችላሉ። በቂ የአጥንት ዕድገት ከሌላቸውና ለጎላ ችግር ካስከተሉ በተለምዶ በቀላል ቀዶ ህክምና ይወገዳሉ። ትንሽ መንጋጋ ካለዎት በመጨረሻ ወይም wisom tooths ጥርሶች ላይ ተጽዕኖ የማድረግ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

ከታችኛው የመጨረሻ መንጋጋ በመቀጠል የላይኛው የመጨረሻ ወይም ዊዝደም ጥርስ በመቀጠልም የላይኛው መንጋጋ የውሻ ክራንቻ ጥርሶች ናቸው።

እነዚህ ጥርሶች በአፍዎ ውስጥ የበለጠ አስፈላጊ ሚና ስለሚጫወቱ ፣ እነዚህ ጥርሶች ከማስወገድ ይልቅ ከተቀበሩበት አጥንት ወደ አፍ እንዲወጡ የሚያበረታቱ ሕክምናዎችን መሞከሩ ይበልጥ ተመራጭ ነው።

የተቀበሩ ጥርሶች እንዴት ይታከማሉ?

የተቀበረ ጥርስ እንዳለዎት ከተጠራጠሩ በተቻለ ፍጥነት የጥርስ ሀኪምዎን ይመልከቱ። የተቀበረ ጥርስ የህመም ምልክት እያመጣ መሆኑን ለማወቅ ሀኪምዎ ጥርሶችዎን መመርመር እና የጥርስዎን ኤክስሬይ ሊወስዱ ይችላሉ። ጥርሱ የተቀበረ ከሆነ የሕክምና ጥቅሞችን እና አደጋዎችን መወያየት ይችላሉ።

የሕክምና አማራጮች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ:

✅ በቦታው መጠበቅ እና መከታተል: የተቀበረ ጥርስዎ ምንም ምልክቶች የማያመጣ ከሆነ ፣ የጥርስ ሐኪምዎ የመጠበቅ እና የማየት አማራጭ ሊጠቁም ይችላል። በዚህ መንገድ ጥርሱን በቀዶ ጥገና ከማስወገድ ይልቅ ፣ ማንኛውም ችግር ሲከሰት ለማየት እንዲችሉ የጥርስ ሀኪሙ በየጊዜው ይከታተለዋል::

✅ቀዶ ጥገና:

የተቀበረ ጥርስ ህመም እና ሌሎች ደስ የማይሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ካጋጠመዎት ፣ የጥርስ ሀኪምዎ በተለይ የተቀበሩ የመጨረሻ የመንጋጋ ጥርሶች ላይ የማውጣት ቀዶ ጥገናን ሊመክር ይችላል። የተቀበረው ጥርስ በሌሎች ጥርሶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ካሳደረ እንዲወጣ ይመክራሉ።

የጥርስ ማስወገጃ ቀዶ ጥገና ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው በቀላል የቀዶ ጥገና ሐኪም ቢሮ ውስጥ እንደ የተመላላሽ ሕክምና ሂደት ነው ፣ ይህ ማለት እርስዎ በታከሙበት ቀን ወደ ቤት መሄድ ይችላሉ። የቀዶ ጥገና ሂደቱ ብዙውን ጊዜ ከ 45 እስከ 60 ደቂቃዎች ይወስዳል ።

በቀን ሁለት ግዜ ጥርሳችን በመብረሽ ጥርሳችንን ከመቦርቦር እንጠብቅ!Telegram: https://t.me/DrMdentalclinic
29/12/2023

በቀን ሁለት ግዜ ጥርሳችን በመብረሽ ጥርሳችንን ከመቦርቦር እንጠብቅ!

Telegram: https://t.me/DrMdentalclinic

ፍንጭት በብሬስ እንዘጋለን
22/12/2023

ፍንጭት በብሬስ እንዘጋለን

Address

In Front Of Teppi Hospital
Tepi
5160

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251931999808

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Mohammed Dental Clinic ዶ/ር መሀመድ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Mohammed Dental Clinic ዶ/ር መሀመድ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ:

Share